ጽ/ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን ማጎልበት እንደሚገባው ተጠቆመ

ጽ/ቤቱ የንግድ ምልክት ጥበቃን አስመልክቶ አዲስ አበባ ውስጥ ለሚገኙ የንግዱ ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላት ተወካዮች የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረክ ሀሙስ የካቲት 20/2010 ዓ.ም በአዝማን ሆቴል አካሄደ፡፡

በተለያዩ የንግድ ዘርፎች ከተሰማሩ ድርጅቶች፣ ከፍትህ አካላት፣ ከንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን፣ ከንግድ ሚኒስቴር እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ለተውጣጡ ተሳታፊዎች በተዘጋጀው በዚሁ መድረክ በንግድ ምልክት ምንነት፣ ጠቀሜታ፣ ከንግድ ስም ጋር በሚኖረው ምስስሎሽና ልዩነት እንዲሁም የጥበቃ ስርዓቱን የተመለከቱ ማብራሪያዎች በንግድ ምልክት ጥበቃ ባለሙያዎች ተሰጥቷል፡፡

በውይይቱ ወቅት ከባለድርሻ አካላት በተለይም ከንግድ ሚኒስቴር፣ ከንግድ ውድድርና ሸማቾች ባለስልጣንና ከፍትህ አካላት ጋር በቅንጅት ከመስራት፣ የዘርፉን ግንዛቤ ከማሳደግ፣ የህግ ክፍቶችን ከመሙላትና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን ከመስጠት ጋር የተያያዙ ሀሳቦች ከተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጓል፡፡    

የንግድ ምልክት ጥበቃና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ትዕግስት ቦጋለ የንግድ ምልክት ምንነት፣ ጠቀሜታና ጥበቃን አስመልክቶ በአብዛኛው የንግዱ ህብረተሰብ ዘንድ ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሀገሪቷ ካሏት በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የነጋዴዎች ብዛት አንፃር ንግድ ምልክታቸውን ለማስመዝገብና ለማስጠበቅ ወደ ጽ/ቤቱ የሚመጡ ድርጅቶችና ግለሰቦች ቁጥር እጅግ አነስተኛ መሆኑን አስረድተው መድረኩ ይህንን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ከታቀዱ የግንዛቤ ማሳደጊያ ፕሮግራሞች አንዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡     


 

 

 

Message from the

Director General

It is indeed a great enchantment for me to address some vital and kernel issues and points with regard to the vision, mission, values and goals of our office- Ethiopian Intellectual Property Office (EIPO) in a nutshell. This is in order to shed lights on our mapped out plan which we all are duty bound to carry to its end using all possible modus operandi . It is a glaring and undeniable fact that the EIPO needs to strive to its utmost capacity to essentially strengthen the national IPR system as a sources of wealth creation and value-addition in its own right, to the benefit of the society and individuals, taking all administrative, technical and legal frameworks into account. Read More...