Skip to Content

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ1

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ2

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ3

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ4

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ5

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ6

Tech Science TV Tech Science TV

TECHIN DOCUMENTARY

Latest News Latest News

የማጃንግ የደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

የማጃንግ የደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ሆኖ በዩኔስኮ ተመዘገበ

በጋንቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ የሚገኘው የማጃንጋ የደን ባዮስፌር ሪዘርቭ ሆኖ በዩኔስኮ መመዝገቡን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ እና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጋትሎዋት ቱት ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት የሰውና ባዮስፌር ፕሮግራም ዓለም አቀፍ አስተባባሪ ካውንስል በመቀመጫው ፈረንሳይ ፓሪስ ከሰኔ 5 እስከ 8 ቀን 2009 ዓ.ም ባካሄደው 29ኛው ጉባኤ የኢትዮጵያ ማጃንግ ደን ባዮስፌር ካውንስሉ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች በማሟላቱ የዓለም አቀፍ የባዮስፌር ጥብቅ ክልል ኔትዎርክ አካል ሆኖ እንዲመዘገብ ውሳኔ ማስተላለፉን በጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል፡፡

በአለም ደረጃ በ120 አካባቢዎች 669 የሚሆኑ ቦታዎች የአለም ባዮስፌር ጥብቅ አካባቢዎች ኔትዎርክ አካል ሆነው የተመዘገቡ ሲሆን ኢትዮፕያም በአራ ብሔራዊ ክልል መስተዳድሮች የሚገኙ አምስት የባዮስፌር ጥብቅ አካባቢዎች ማስመዝገቧን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

የማጅንግ ባዮስፌር ሪዘርቭ ሁለት መቶ ሃያአራት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያአምስት (224,925) ሄክታ ስፋት ያለው ሲሆን ከ550 በላይ እየተመናመኑ የሚገኙ ተክሎች፣ 33 አጥቢ እንስሳቶች፣ 130 አእዋፍት ፣ 20 ተሳቢ እንስሳቶች እንዲሁም ከፍተኛ አደጋ ላይ ያሉ ተብለው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተመዘገቡ 39 ዝርያዎች ይገኙበታል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

በመጨረሻም ከጋዜጠኞች እና ተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ሚኒስትሩ እንዲሁም የመስተዳድሩ ፕሬዝዳንት ምላሽ ሰተዋል፡፡

 


// ]]>