Skip to Content

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ1

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ2

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ3

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ4

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ5

ቴክ-ሳይንስ ቅጽ6

Tech Science TV Tech Science TV

TECHIN DOCUMENTARY

Latest News Latest News

የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት የህክምና ፕሮፌሰር

ደስተኛ ለመሆን ብዙ ጥረት አናድርግ ፡፡ ጥረታችን ደስተኝነታችንን ሊያጠፋ ይችላልና

ብዙዎቻችን ስራችንን አጥብቀን እንሰራልን እያንዳንዱን እንቅስቃሴያችንን ደስተኛ ያረጉናል ብለን ያሰብነው ግብ ላይ ለመድረስ እንታትራለን፡፡ ነገር ግን ጥያቄው ይህ የጠበቅነውን ውጤት ያመጣልናል ?

አንዳንዴ እንዲህ ያጋጥመናል ወደ ዩንቨርስቲ ወይም ወደ ኮሌጅ ገብቼ ይህን ዲፕሎማ ወይም ድግሪ ባገኝ ደስተኛ ሆናለው እንላለን ከዘም እንመረቃለን ነገር ግን አሁንም ደስተኝነት ከኛ እንደራቀ ነው፡፡ እንቀጥልና ድግሞ ይህን ስራ ካገኘው እንላለን ያንን ለማድረግ እንጥራለን ከዛም ያለንበት ቦታ እንደረሳለን ከደረስን በኋላ ደግሞ ለዚህ ነው የለፋነው እንላለን፡፡

ደስተኛ መሆንን እንደ ግብ መውሰድ ልክ እንደወረርሽኝ እየሆነ ነው፡፡ ደስተኛ ድብልቅልቅ (abstract) ፣ የሚፈስ (fluid) እንዲሁም ተለዋዋጭ (fickle) ሀሳብ ነው፡፡

ጥናቶች ግን የሚያሳዩት  

  • ደስተኛ ለመሆን ብለን ብዙ ሀይላችንን ደስተኝነትን በመፈለግ ማጥፋት ደስተኛ ከማድረግ ይልቅ እንደውም ወደ መከፋት እና አለመደሰት ሊወስደን ይችላል፡፡ ሰዎች በአጠቃለይ ደስተኛ ለመሆን ይወዳሉ፣ ደስተኛ ለመሆን ይሞክራሉ አንዲሁም የበለጠ ደስተኛ ለመሆን ይፈልጋሉ አሁን ባሉበት ሁኔታ በአግባቡ ደስተኛ ሆነው ሳሉ፡፡
  • ጥናቶች እንዳመለከቱት አራሳችንን ደስተኛ ለማድረግ ከሆነ ግብ ጋር አያይዘን እዛ ላይ ለመድረስ ጥረት የምናደርግ ከሆነ የን ያሰብንበት ቦታ ለመድረስ በቂ ጊዜ እንደሌለን ልናስብ እንችላለን፡፡ እናም እዛ ያቀድንበት ቦታ ላይ መድረስ አድሉ ማነሱን መሰማት እኛን አሁን ባለንበት ደስተኛ እንዳንሆን ያደርገናል፡፡ ጊዜ ደስታን መከታተላችንን (the pursuit of happiness) ሊያጠፋብን ይችላል ነገር ግን ይህ የሚሆነው ደስተኝነት ግብን የሚከተል ፍለጋ ከሆነ ነው፡፡

ስለዚህ ተመራማሪዎቹ የሚጠቁሙን

  • ደስተኝነታችንን ለመፈለግ ከመጨነቅ ይልቅ ህይወትን ለማጣጠም ጊዜ መስጠት ይኖርብናል፡፡
  • ሰዎች ደስታን መከተል የሚያበቃ ግብ አለመሆኑን አይደለም ብለው ከመጨነቅ ይልቅ እያንዳንዱ ትንሽ ሽኬት የራሱ የሆነ ደስታ እንዳለው አውቀው ደስታን ማጣጣም አለባቸው፡፡

ደስተኛ ሁኑልኝ ያላችሁ፡- Medical News Today

ፕሮፌሰሯ ጉዟቸውን ሲያስረዱ “ሜዲካል ዶክተር ሆኖ እንደገና ተመልሶ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት ስሆን አንድ የመጀመሪያ ብቸኛ ሴት ነው የነበርኩት፡፡ ወደ 23 ወንዶች ነበር የነበሩት፡፡ ትምህርት ክፍሉ ውስጥ ተወዳድሬ ነው የቀረሁት፡፡ ተመልሼ የገባሁት በቀለም ሲኮተኩቱኝ የቆዩ አስተማሪዎቼ ጋር ነው፡፡ እንግዲህ ከባድ እና ፈታኝ ነው ግን በዚህ ልክ እንደገባሁ የእኔ የበላይ አለቃ የነበሩት አሁን በህይወት የሌሉት ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድር ወደ ምርምሩ ዘርፍም እንደገባ አደረጉኝ፡፡ ቶሎ ነው፣ በገባሁ በሶስተኛ ቀን ነው ወደ ምርምር ዘርፍ ሀሳቤ እንዲያደላ ያደረግሁት፡፡ ስለዚህ እኔ በቃ አንዳንድ ተግዳሮቶች ቢኖሩም ግን አማራጭ መንገዶችን በማየት ማለፍ ይኖራልብለዋል፡፡

እንዲህ የተጀመረው የፕሮፌሰር የወይንሐረግ የምርምር ስራ በርካታ ውጤቶቸ የተመዘገቡበት ሆኗል፡፡ ወደ 65 ገደማ የምርምር ጽሁፎችን ማዘጋጀታቸውን የሚናገሩት መምህሯ 52 የሚሆኑቱ በተለያዩ የምርምር መጽሔቶች (ጆርናሎች) ላይ መታተማቸውን ያስረዳሉ፡፡ አብዛኞቹ የጥናት ስራዎቻቸው በስኳር በሽታ እና ተያያዥ የሆርሞን ህመሞች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ስፔሻላይዝድ ያደረጉበት ሙያቸው እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስት የሆኑት ፕሮፌሰር የወይንሐረግ  በስኳር ህመም እና ሆርሞን ህመሞች ላይ ህክምና እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ፕሮፌሰር የወይንሐረግ በህብረተሰቡ ዘንድ ስለስኳር ህመም ያለው ግንዛቤ ያደግ ዘንድ ሰለበሽታው የሚያወሳ መጽሐፍ በአማርኛ ቋንቋ አሳትመዋል፡፡ 10 ዓመት በፊት ለንባብ የበቃው ይህ መጽሐፍ 11 ሺህ ቅጂ ተባዝቶ ተሰራጭቷል፡፡ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢም ለጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲውል መለገሳቸውን ይናገራሉ፡፡ መጽሐፉን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ጎን ለጎን የስኳር ህመም እና የህሙማን እንክብካቤ ምን እንደሚመስል የሚገመግም ጥናት አካሄደዋል፡፡ ይህ በአዲስ አበባ በሚገኙ አምስት ሆስፒታሎች እና 21 ጤና ጣቢያዎች ላይ የተካሄደው ጥናትም ሀገር ውስጥ በሚታተም ጆርናል ላይ ለንባብ በቅቷል፡፡ 

አንጋፋዋ ምሁር ከምርምር ጋር ያላቸው ቁርኝት በዚህ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ የሚያስተምሯቸው ወጣቶች ተመራማሪዎች እንዲሆኑ ያግዛሉ፡፡ በጥናቶቻቸው ላይ በመሳተፍም የምርምር ውጤቶችን በጋራ ያሳትማሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍል ላለፉት 25 ዓመታት እያስተማሩ የሚገኙት ፕሮፌሰር የወይንሐረግ መምህርነታቸውን እንደሚወዱት ይናገራሉ፡፡

ፕሮፌሰር የወይንሐረግ በማስተማሩ፣ በምርምሩ እና ህክምናው ብቻ ተወስነው አልቀሩም፡፡ ያላቸውን የተጣበበ ጊዜ እንደምንም አብቃቅተውም ቢሆን በተለያዩ የሙያ ማህበራት በቦርድ እና በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት ይሳተፋሉ፡፡ አባል በሆኑበት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት እስከመሆን ደረጃ ደርሰዋል፡፡ ከተመሰረተ 56 ዓመቱን በያዘው በዚህ ማህበር ሊቀመንበርነቱን በመያዝም የመጀመሪያዋ ሴት ሆነዋል፡፡ በኃላፊነት ቦታው ከአንድም ሁለት ጊዜ ተመርጠው አገልግለዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ከማስተማር ስራቸው ለተወሰነ ጊዜ ፍቃድ በመውሰድ ጭምር ማህበሩን አንድ እርምጃ ለማራመድ ሞክረዋል፡፡ ይህን ጥረታቸውን ከግምት ያስገባው ማህበሩ ባለፈው ዓመት ሸልሟቸዋል፡፡

ዘርፈ ብዙዋ ምሁር ተሳትፏቸው በርካታ፣ አገልግሎታቸውም በየመስኩ ቢሆንም ለእርሳቸው ትልቁ ነገር የሰው ህይወት ማትረፍ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ከህይወት በላይ ምንም ነገር የለምናሲሉም ያጠቃልላሉ፡፡

ምንጭ፡- የጀርመን ድምጽ (Deutsche Welle )

 


// ]]>